መዝሙር እንዘምር እናመስግን

የስላሴን መንበር

የስላሴን መንበር
የስላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሀል ሚካኤልን ከፊት
አዕላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍርሀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት

የስላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ
በፅድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ (2)

አዝ ....

የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር
ሲያወድስ ይኖራል የስላሴን መንበር
ፅድቅና ርህራሄ የተሞላ ሰማይ
እግዚያብሄር ያድለን በትንሳኤ እንድናይ